በኢትዮጲያና በኤርትራ መካከል ግንኙነቶችን ለማሻሻል የወቅቱ የኢትዮጲያ መንግስት ፖሊሲ መቀየር አለበት አልያም ስራአቱ መቀየር አለበት ይላሉ አቶ ኤርምያስ ለገሰ፣ የቀድሞው የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚንስተር ደ-ኤታ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ቪዥን ኢትዮጲያ (Vision Ethiopia) ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት (ESAT) ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያና ኤርትራ ወቅታዊና የወደፊት ግንኙነት” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት የውይይት መርሃ ግብር በቅርቡ እዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሂዷል።
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት፥ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ፥ የኢትዮጵያና የኤርትራ ማህበረሰብ መሪዎች ያላቸው ሚናና፥ የኃያላን መንግሥታትና ያካባቢው ኃይሎች በአፍሪካ ቀንድ ያላቸው ፍላጎት ምንድነው በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶችን ሰምተናል።
ዛሬ በሦስተኛውና በመጨረሻው ዝግጅት የአንድ አስረጂና ከተለያዩ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ይቀርባሉ።
አዘጋጁ በሥፍራው የነበረው ሰሎሞን ክፍሌ ነው። ዘገባውን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጲያና የኤርትራ የወቅቱና መፃኢ ግንኙነት