በትናንትናው ዕለት የአሜሪካው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ የተላለፈው እና “ፕሬዝደንት ባይደን፤ ልጃቸው ሃንተር ባይደን በውጪ ሀገራት ካለው የንግድ ሽርክና ተጠቃሚ ናቸው” በሚል ምርመራ እንዲደረግባቸው የወጣው ትዕዛዝ፣ በትረምፕ እና በቀኝ ዘመም ደጋፊዎቻቸው ለወራት ሲቀነቀን የነበረ ነው ተብሏል።
“ፕሬዝደንት ባይደን፤ ልጃቸው ሃንተር ባይደን በውጪ ሀገራት ካለው የንግድ ሽርክና ተጠቃሚ ናቸው”
የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በእ.አ.አ 2019 መጨረሻ ላይ ዩክሬን እና ሌሎችን ሀገራትን በመጠቀም የተቀናቃናቸውን ጆ ባይደን ስም ለማጠልሸት ሞክረዋል በሚል በአሜሪካ ም/ቤት ተከሰው ነበር።
ከአራት ዓመታት በኋላ፣ ሪፐብሊካን፣ ጆ ባይደንን ለመክሰስ ምርመራ እንዲካሄድ በአፈ ጉባኤው በኩል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህም በትረምፕ እና ደጋፊዎቻቸው ለረጅም ግዜ ሲገፋ የነበረ አጀንዳ ነው ተብሏል።
ከትረምፕ ክስ በተቃራኒ፣ በባይደን ላይ የሚሰማው ክስ ምንም ማስረጃ የለውም ሲል የኤኤፍ ፒ ዘገባ አመክቷል።
SEE ALSO: የአሜሪካ ም/ቤት በባይደን ላይ የሙስና ምርመራ እንዲያካሂድ አፈ ጉባኤው አዘዙየምክር ቤቱ የቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ጄምስ ኮመር፣ ባይደን ጥፋት ለመፈጸማቸው ምንም ማስረጃ የላቸውም ሲል ሪፖርቱ አክሏል።
ኮመር፤ ስም ሳይጠቅሱ፣ የ “ባይደን የቤተሰብ ዓባላት” እና “ሽርኮቻቸው” 20 ሚሊዮን ዶላር በውጪ አካላት እንደተከፈላቸው ይናገራሉ።
የጆ ባይደን ልጅ ሃንተር ባይደን በቻይና፣ ካዛክስታን፣ ሮማኒያ እና በሌሎችም ሀገራት የንግድ ግንኙነት አላቸው። በማካርቲ ትናንት የቀረበው የምርመራ ጥሪ ግን ‘በሪስማ’ በተሰኘው የዩክሬን የኃይል ኩባንያ ላይ ያተኮረ መሆኑን ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።
የም/ቤቱ በርካታ ኮሚቴዎች ለውንጀላው ማስረጃ ገና እንዳላቀረቡ የቪኦኤዋ ካትሪን ጂፕሰን ዘገባም አመልክቷል።