ትረምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተረፉ

  • ቪኦኤ ዜና

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

Your browser doesn’t support HTML5

ትረምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተረፉ

እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጣ ዶናልድ ትረምፕ በሁለት ወራት ዕድሜው ለሁለተኛ ዙር ከተቃጣባቸው ያልተሳካ የግድያ ሙከራ ተርፈዋል። በትላንትናው ዕለት የተፈጸመው እና ተጠርጣሪ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ሥር የዋለበት ምርመራ ሂደት በፌድራሉ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ መሪነት እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።

ድንገቱ ቀድሞውንም ከፍተኛ ትኩረት በሳበው እና ባልተጠበቁ አስገራሚ እንቅስቃሴዎች በተመላው የምርጫ ሂደት፤ አሜሪካውያን ሌላ ያልተጠበቀ ሁኔታ ገጥሟቸዋል። የአሜሪካ ድምጿ የዋይት ሀውስ ጋዜጠኛ አኒታ ፓውል ከዋሽንግተን ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።