በትግራይ ክልል ከ20ሺሕ በላይ ተማሪዎች በረኀብ ምክንያት ትምህርት አቋረጡ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ከ20ሺሕ በላይ ተማሪዎች በረኀብ ምክንያት ትምህርት አቋረጡ

በትግራይ ክልል በ57 ወረዳዎች በረኀብ ምክንያት 20ሺሕ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ይህ የተማሪዎቹ አኃዝ፣ በተገባደደው የካቲት ወር ብቻ የተመዘገበ እንደሆነ ቢሮው ገልጿል፡፡

በቂ የርዳታ ምግብ በአፋጣኝ ካልደረሰና በትምህርት ቤቶች የምገባ መርሐ ግብር ካልተጀመረ፣ ለመዘጋት የተቃረቡ ትምህርት ቤቶች ብዙዎች እንደኾኑ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረ እግዚአብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

SEE ALSO: በትግራይ “ከባድ ረኀብ አንዣቧል” ያሉት ጌታቸው ረዳ የዳያስፖራውን ድጋፍ ተማፀኑ

ዓለም አቀፉ የሕፃናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ፣ በክልሉ በመጠለያ ማዕከላት ከሚገኙ ሚሊዮን ሰዎች 20 በመቶ የሚኾኑት ሕፃናት ለምግብ እጥረት እንደተጋለጡ አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።