ዶ/ር ሪያክ ማቻር፡- 2016 ዓ.ም. በደቡብ ሱዳን የሰላም ዓመት ይሆናል

  • ቆንጂት ታየ

ዶ/ር ሪያክ ማቻር ፋይል ፎቶ[አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo]

ዶ/ር ሪያክ ማቻር አዲሱ የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. ለደቡብ ሱዳን የሰላም ዓመት ይሆናል በማለት ለሃገሪቱ ህዝብ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚደንት ያሁኑ የአማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር አዲሱ የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. የሰላም ዓመት ይሆናል ስሉ ለሃጋሪቱ ህዝብ ኣረጋገጡ።

ሽምቅ ተዋጊ ቡድናቸው ህዝቡ ከሃያ ኣንድ ወራት በፊት የርስ በርስ ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ ኣንስቶ የተጠማውን ሰላም እንዲያገኝ ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

የሳቸው ቡድን ባለፈው ነሃሴ የተፈረመው የሰላም ውል ተግባራዊነት እንዲጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኑን የገልጹት ማቻር፣ ፕሬዚደንቱ ምክክር ሳይደረግበት ሃያ ስምንት አዳዲስ ክፍላተ ሃገር መፍጠራቸው የውሉን ተግባራዊነት ያደናቅፋል ብለዋል።

ትናንት ፕሬዚደንት ማቻር ክፍላተ ሀገሩን ያቋቋምናቸው በህዝቡ ፍላጎት ስለሆነ በሽግግሩ ህገ መንግስትም መሰረት በመሆኑ ተከላከሉለት ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ጥሪ አሰምተዋል።