ሰለ ኦሮምያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት

  • እስክንድር ፍሬው

Ethiopia's State of Emergency

የኦሮምያና የሶማሌ ክልል አዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች በታጣቂዎች ለሚፈፀምው ጥቃት መፍትሄ ለማስገኘት በአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስትና በሁለቱ ክልሎች ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

ከኦሮምያ አዋሳኝ ቦታዎች የሚወጡ ያሉዋቸው ታጣቂዎች በክልላቸው አዋሳኝ ወረዳዎች ጥቃት እየተፈፀመ መሆናቸውን የተናገሩት የሶማሌ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽንስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማዔል ናቸው፡፡ ታጣቂዎቹ የኦሮምያን መንግሥት ሕዝብንና ተቋማቱን የማይወክሉና በውጭ ያሉ ፀረ ሠላም ኃይሎች የሚመሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች ጥቃት የሚፈፅሙ ኃይሎችን በተመለከተ የሁለቱ ክልላዊ መንግሥታት ግምገማ ተመሳሳይ አለመሆኑ ይታያል፡፡ ጥቃት እየፈፀሙ ያሉት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚነሱ ነገር ግን ሕዝቡንም ሆነ ክልላዊ ተቋማቱን የማይወክሉ ታጣቂዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሰለ ኦሮምያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት