ጋዜጠኞች እንዲገደሉ ለአል-ሸባብ ጠቁሟል የተባለ ጋዜጠኛ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት

Your browser doesn’t support HTML5

ሐሰን ሀናፊ የተባለ ጋዜጠኛ አምስት ጋዜጠኞችን ለአልሸባብ በመጠቆም እንዲገደሉ አስደርጓል በሚል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡ ጋዜጠኛው እ.አ.አ ከ 2007እስከ 2011 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ የሥራ ባልደረቦቹ የኾኑ ጋዜጠኞች ላይ መጠቆሙ ተረጋግጦበታል ሲል መቋዲሾ ውስጥ የሚገኝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ፈርዶበታል፡፡