አዲስ ጥናት፡- “አይስስ በአሜሪካ ከትዊተር ልውውጥ እስከ ራቃ”

እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚልው ጽንፈኛ ቡድን በዋሽንግተን ጥቃት እንደሚፈጽም በቪድዮ እንዳስጠነቀቀ ይታወሳል። ይህ ፋይል ፎቶ ከቪድዮው የተገኘ ነው።

“አይስስ በአሜሪካ ከትዊተር ልውውጥ እስከ ራቃ” ወይም “ISIS in America: From Retweets to Raqqa” በሚል ርእስ የወጣው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲት ፕሮግራም ጥናት አሜሪካ ውስጥ ስላሉት የሱኒ እስላም የሆነውን ጽንፈኛ ቡድን ስለሚደግፉት አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው ሆኖም ፈጣን ተግባር ስለሚያከናውኑት አሜሪካውያን ወይም ደግሞ በአሜሪካ ስለሚኖሩት ግለሰቦች ግንዛቤ ለማግኘት ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ (United States) ውስጥ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚልውን ቡድን የሚደግፉት ሰዎች ምን አይነት እንደሆኑ ለማወቅ የተደረገ አዲስ ጥናት መካከለኛ እድሚያቸው 26 አመት፣ 86 ከመቶ ወንዶች፣ ፕሮፓጋንናዳውን ለማግኘትና ለማስፍፋት በአብዛኛው ትዊተርና በሌላ የማህበረሰባዊ ሚድያ የሚጠቀሙ ከመሆናቸው ሌላ ብዙም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ይገልጻል።

“አይስስ በአሜሪካ ከትዊተር ልውውጥ እስከ ራቃ” ወይም “ISIS in America: From Retweets to Raqqa” በሚል ርእስ የወጣው ጥናት የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲት ፕሮግራም ሲሆን አሜሪካ ውስጥ ስላሉት የሱኒ እስላም የሆነውን ጽንፈኛ ቡድን ስለሚደግፉት አንስተኛ ቁጥር ስላላቸው ሆኖም ፈጣን ተግባር ስለሚያከናውኑት አሜሪካውያን ወይም ደግሞ በአሜሪካ ስለሚኖሩት ግለሰቦች ግንዛቤ ለማግኘት ነው።

ጥናቱን ያካሄዱት ሰዎች ለስድት ወራት ያህል የፍርድ ቤት ሰነዶችን፣ የማህበራዊ ሚድያ ጽሁፎችን፣ የዩናይትድ ስቴትስ (United States) ባለስልጣኖች መግለጫዎችን ሲመረምሩ የቆዩ ቢሆንም የጽንፈኛው ቡድን ደጋፊ አሜሪካዊን ለይተው ለማዋቅ እንደተቸገሩ አስገንዝበዋል።

እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ (United States) ውስጥ ከአይስስ (ISIS)ጋር የተሳሰሩ ተግባሮች የሚፈጽሙት ሰዎች በዘር፣ በመደብ፣ በትምህርትና በቤተሰብ የጀርባ ታሪክ እንደሚለያዩ ዘገባው ጠቁሟል። አላማቸውም የተለያየ እንደሆነ ዘገባው አክሎ ገልጿል። ዜናውን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አዲስ ጥናት፡- “አይስስ በአሜሪካ ከትዊተር ልውውጥ እስከ ራቃ”