በአንድ የብራስልስ አፓርትመንት ውስጥ ባካሄዱት አሰሳ፣ እአአ ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ተጠርጣሪ ነው ያሉትን ሰው አሻራ ማግኘታቸውን ዛሬ ዐርብ አስታወቁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የቤልዥግ ፖሊሶች፣ በአንድ የብራስልስ አፓርትመንት ውስጥ ባካሄዱት አሰሳ፣ እአአ 2015 ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ተጠርጣሪ ነው ያሉትን ሰው አሻራ ማግኘታቸውን ዛሬ ዐርብ አደረጉ።
የቤንዢግ ፌዴራላዊ መንግሥት ዐቃቤ ህግ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ መርማሪዎች ሳላሕ አብደሰላም (Salah Abdeslam) የተባለውን ተጠርጣሪ አሻራና፤ ምናልባትም ፈንጂዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ሦስት የእጅ ሥራ የሆኑ ቀበቶዎችን አግኝተዋል። በዚሁ መኖሪያ ህንፃ ውስጥ መርማሪዎቹ የፈንጂ ምልክቶችንም እንዳገኙ ተናግረዋል።
ተጠርጣሪው አብደሰላም (Abdeselam) ወደተጠቀሰው አፓርትሜንት መቼ እንደገባ ግልጽ አለመሆኑን ያመለከተው የዐቃቤ ህጉ ቃል-አቀባይ፣ ባለሥልጣናቱት ደግሞ አሁን የተገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ ስለምን አንድ ወር ሙሉ እንደቆዩ አላብራራም።