የተወለደችው በትግራይ አድዋ ከተማ ነው። የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አዲስ አበባ በሚገኘው በቴጌ መነን ት/ቤት ከጨረሰች በኃላ ከአዲስ አበባ የስነጥበብ ትምህርት ቤት በስዕል ስራ ትምህርቷን አጠናቃለች። በመቀጠልም በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ በሚገኘው ሉተራል ዩኒቨርስቲ የስዕል ትምህርቷን ለአራት አመት ቀጥላ ተምራለች። ከሃምሳ ጊዜ በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለብቻዋና ከሌሎች ሰአሊዎች ጋር በጋራ በመሆን አሳይታለች።
ከልጅነቷ በስራዎቿ በመደነቅና በመሸለም ስኬቷን የተቀዳጀች ሴት አርቲስት ናት ደስታ ሃጎስ። በተለያዩ አውሮፓ ሃገራት እንዲሁም በአሜሪካ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለረጅም አመታት አሳይታለች። ታዲያ በነዚህ የስኬት የስዕል ኤግዚቢሽኖች መሃል አንድ የማይረሳ አሳዛኝ ክስተት አጋጥሟታል፤ ወደ ሰላሳ የሚጠጉ የስዕል ስራዎቿን ለዕይታ ለማቅረብ ወደ ጀርመን ስትጓዝ ለኤግዚቢሽኑ የታሰቡት የስዕል ስራዎቿ በሙሉ በመንገድ ላይ ጠፉ። እስከዛሬም የደረሱበት አልታወቀም።
በቅርቡ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ በዩናይትድ ስቴትስ በፍሎሪዳ ማያሚ ከተማ፤ ኢትዮጵያ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ የሆነው አለም አቀፉ አመታዊ የስዕል ኤግዚቢሽን ላይ “ትዝታ ኤግዚቢሽን” በሚል ስያሜ ከሌሎች አምስት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ወክላ የስዕል ስራዎቿን ለዕይታ አቅርባ አድናቆትን አትርፋለች።
ከመስታወት አራጋው ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጋለች። ከታች የሚታየውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5