በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የኦሮምያን የወቅቱን ሁኔታ አስመልክቶ ማክሰኞ ማብራሪያዎች በተሰሙበት ወቅት የተናገሩ የአሜሪካው ኮንግረስ አባላት ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ሰሞኑን እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።
ሰልፉ ላይ የወጡት በአሜሪካ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ቁጥር ከሁለት ሺህ በላይ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ለመገናኛ ብዙኃን በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ የወቅቱን የኦሮምያን ሁኔታ የሚመለከቱ ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
በዚህ ማብራሪያ ወቅት ላለፉት አርባ ዓመታት ኢትዮጵያን እንደነበሩና ኢትዮጵያንም በደንብ እንደሚያውቋት የተናገሩት የሰብዕናና የማኅበረሰብ ጥናት ባለሙያ ቦኒ ሆኮምብ “በኢትዮጵያ ግዙፉና አብላጫ የሆነው የኦሮሞ ማኅበረሰብ እንደ ኅዳጣን ሆኖ ሲኖርና ሲያዝ አይቻለሁ” ብለዋል።
ቀደም ሲል የተናገሩት የሕዝብ እንደራሴ ቤቲ ማኮለም ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮምያ ክልል እየተካሄደ ነው ላሉት ያላቸውን ሥጋት ገልፀዋል።
“ሰላማዊ ተቃዋሚዎች እየታሠሩ ነው፤ የሥቃይ አያያዝ እየደረሰባቸው ነው፤ እየተገደሉ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በተጠያቂነት ሊያዝ ይገባዋል፤ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና እንዲያቆም ከኮንግረሱና ከኦባማ አስተዳደር ግፊት ሊደገግበት ይገባል” ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5