ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ የሚያካሂደውን ግድያ ያቁም፣ ኦሕዴድ ሥልጣን ይልቀቅ፣ ለተጎዱ ካሣ ይከፈል የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን የያዙ ነበሩ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ የተፈጠረውን ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሚጠይቁ ሰልፎች ዋሺንግተን ዲሲ ላይና አውሮፓ ውስጥ ደግሞ በርሊን ተካሂደዋል።
አዘጋጆቹ አንድ ሺህ ሰው ወጥቶበታል ባሉት የዋሽንግተኑ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተውበታል።
ሰልፉ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤትና መኖሪያ ዋይት ሃውስ ተጀምሮ ወደ ሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቀጥሏል። በርሊን ላይ ላይም የወጡት ሰልፈኞች ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች የተጠራሩ ሲሆኑ ሥነ-ሥርዓታቸውን ያከናወኑት በሃገሪቱ ፓርላማና በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ፊት ለፊት እንደሆነ ታውቋል።
ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ የሚያካሂደውን ግድያ ያቁም፣ ኦሕዴድ ሥልጣን ይልቀቅ፣ ለተጎዱ ካሣ ይከፈል የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን የያዙ ነበሩ።
Your browser doesn’t support HTML5