የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ

  • መለስካቸው አምሃ
እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ።

እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። የማረሚያ ቤቱ ተወካይ አቤቱታውን አስተባብለዋል። ተከሳሾቹ በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ ለሌላ ጊዜ ተቀጥረዋል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ሙሉውን ዘገባ ከመለስካቸው አመሃ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ

የኢትዮጵያው ፌዴራል ዐቃቤ ህግ፣ 33 ሰዎችን በአገር ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (የኦነግን) ድርጅታዊ ህዋስበመመሥረት፣ በመምራትና አባላት በመሆን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል፣ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሠረተባቸው። ፍርድ ቤቱም፣ ተከሳሾቹ መልስ እንዲሰጡ በማለት ተለዋጭ ቀጠሮሰጥቶ ተነስቷል። መለስካቸው አምሃ ተጨማሪ ዝርዘር ልኳል።

Your browser doesn’t support HTML5

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ