በናይጄሪያ እየደረሰ ባለው የጎርፍ አደጋ በሃገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ የሚገኝ የአንድ እስር ቤትን ግድግዳ ማፍረሱን ተከትሉ፣ 281 እስረኞች ማምለጣቸው ታውቋል።
ከቀናት በፊት በፈረሰ ግድብ ምክንያት በደረሰ የጎርፍ አደጋ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።
SEE ALSO: በናይጄሪያ ጎርፍ 30 ገድሎ 400ሺሕ አፈናቀለባለፈው ሳምንት ማይዱጉሪ በተባለው እስር ቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ለማስወጣት የፀጥታ አስከባሪዎች ሲገኙ፣ እስረኞቹ ቀድሞውኑ አምልጠው መገኘታቸውን የናይጄሪያ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ትላንት እሁድ አስታውቋል።
ጎርፉ የእስር ቤቶቹን ግድግዳ እንዲሁም የጠባቂዎቹንና የሠራተኞቹን ቢሮዎች ማፍረሱን አስተዳደሩ ጨምሮ አስታውቋል።
ጉርፍ በመላው ምዕራብ አፍሪካ ባደረሰው ጉዳት 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ለችግር ተጋልጠዋል።