በቅርቡ ከእስር የተለቀቀው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀና ሌሎች ሁለት ወጣቶች ታሰሩ

የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

ቀደም ሲል በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች አንዱ የሆነው ናትናኔል ፈለቀ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ አባል ያልሆኑ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ አለም ደስታ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። የናትናኤል ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን ማምሻውን አነጋግረናቸዋል።

አቶ አመሐ መኮንን ናትናኤልን በዛሬው ዕለት ማግኘታቸውን ጠቅሰው ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ናትናኤል ፈለቀ ፣ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ አለም ደስታ የተባሉ ወጣቶች ሲቪል በለበሱ የፓሊስ አባላት ተይዘው መታሰራቸውንና "በላሊበላ ሬስቶራንት ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር በመሆን ድምጹን ከፍ አድርጎ ለእልቂቱ መንግስት ተጠያቂ ነው በማለት ሌሎችን ለአመጽ ቀስቅሷል" በሚል ክስ እንደቀረበባቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ጽዮን ግርማ አቶ አመሐ መኮንንን ማምሻው አነጋግራቸዋለች።

Your browser doesn’t support HTML5

በቅርቡ ከእስር የተለቀቀው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀና ሌሎች ሁለት ወጣቶች ታሰሩ