እንግሊዛውያኑ ሮሊንግ ስቶንስ አለም አቀፍ ተወዳጅ ሙዚቀኞች

ፋይል ፎቶ፡ሮሊንግ ስቶንስ በ1960ዎቹ ታዋቂ የሮክ እና ሮል ሙዚቀኞች

ፋይል ፎቶ፡ሮሊንግ ስቶንስ በ1960ዎቹ ታዋቂ የሮክ እና ሮል ሙዚቀኞች

እንግሊዛውያኑ ወጣት ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones) እ.አ.አ በ1960ዎቹ በሮክ ኤንድ ሮል (Rock & Roll) የሙዚቃ ስልት የተለየ አድማጭ ያገኙ ተወዳጅ ሙዚቀኞች ነበሩ።

ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones) ጨምሮ ዘ ሁ (The Who) እና ዝ ኪንክስ (The Kinks) በጊዜው በግንባር ቀደምትነት ይታወቃሉ። ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones) ከሌሎቹ የሙዚቃ ባንዶች የተለየ የሚያደርጋቸው የአባላቱ ረጃጅም ፀጉርና የአሜሪካንን የብሉዝ ስልት በሙዚቃ ስራቸው ውስጥ ያካትቱ ስለነበር ነው። ሙዚቃቸው ዘመን ሳይሽረው እስከአሁን ይደመጣል፣ በተለያዩ መድረኮችም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በማሳየት ላይ ናቸው፣ የቀድሞውንም አዲሱንም ትውልድ አሁንም ሙዚቃቸውን እንደ አዲስ ያደምጣል፤ በሙዚቃቸው ይደሰታል።

በሙዚቃው አለም ለረጅም ጊዜ እንደመቆየታቸው ስለሙዚቃ ስራቸውና ስለህይወት ተሞክሯቸው ተደጋግሞ ተነግሯል። የፋኢዛ ኤልማስሪ (Faiza Elmasry) የቅርብ ጊዜ መፀሃፍ ደግሞ በተለየ የሙዚቀኞቹን ሚክ ጃገር(Mick Jagger)፣ ኪት ሪቻርድስ (Keith Richards)፣ ሮኒ ዉድ (Ronnie Wood), ቻርሊ ዋትስ (Charlie Watts) እና ቢል ወይማን(Bill Wyman) ታሪክን በስፋትና በጥልቀት ይዞ ቀርቧል።

የመፅሃፉ ርዕስ ካውንቲንግ ዳውን ዘ ሮሊንግ ስቶንስ (Counting down the Rolling Stones) ይሰኛል። በሙዚቃ አድማጮች ተወዳጅ የሆኑት 100 የሚሆኑ ሙዚቃዎችም ከመፅሃፉ ጋር አብረው ተካተዋል።

ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሮሊንግ ስቶንስ (Rolling Stones)