ዶ/ር መረራ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

  • መለስካቸው አምሃ

ዶ/ር መረራ ጉዲና

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩና የክሥ መቃወሚያ ካላቸውም እንዲያቀርቡ አዝዟል፡፡

ዶ/ር መረራ በፍርድ ቤቱ ውሣኔ ማዘናቸውን ለችሎቱ ገልፀዋል፡፡ ጠበቃቸው በውሣኔው ላይ ይግባኝ እንደሚሉ አስታውቀዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ መድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ዶ/ር መረራ ጉዲና በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስ መብታቸው እንዲከበርና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው አንዲከታተሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀረ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5