1. ትክክለኛውን መንገድ ለማምጣት ጊዜው አሁን ነው
"The time is always right to do what is right."
2. ጨለምተኝነት ጨለማን አያጠፋም፤ ብርሃን እንጂ! ጥላቻ ጥላቻን አያጠፋም፤ ፍቅር እንጂ
"Darkness cannot drive out darkness; only light can do that. Hate cannot drive out hate; only love can do that."
3. በአንድ ቦታ ፍትህ ሲጠፋ፤ በዓለም ዙሪያ ፍትህ ይጠፋል
"Injustice anywhere is a threat to justice everywhere."
4. ከሞትም በላይ ሞት፤ ያሰብንውን በነጻነት ሳንናገር ጽምታን መምረጥ ነው
"Our lives begin to end the day we become silent about things that matter."
5. በፍቅር እንቆይ! ጥላቻ ብዙም የማያራምድ ሸክም ነው
"I have decided to stick with love. Hate is too great a burden to bear."
6. እምነት ማለት የደረጃውን ጫፍ ሳያዩ ሽቅብ መውጣት ነው
"Faith is taking the first step even when you don’t see the whole staircase."
7. ይቅር ባይነት አልፎ አልፎ የምናደርገው ሳይሆን የለት ተለት የኑሮ አመለካከት ነው
"Forgiveness is not an occasional act; it is a constant attitude."
8. በህይወታችን ውስጥ ወሳኝና አስፈላጊ ጥያቄ፤ ለሌሎች ሰዎች ምን አደረግን የሚለው ነው
"Life's most persistent and urgent question is, 'What are you doing for others?''
9. ለዓለማችን ጸር ከሆኑ አስተሳሰቦች አለማወቅና ታስቦበት የሚደረግ የድንቁርና አስተሳሰብ የሚበልጥ የለም
"Nothing in the world is more dangerous than sincere ignorance and conscientious stupidity."
10. እልቁ መሳፍርት የሌላቸው ቅስም የሚሰብሩ ጉዳዮች እንዳሉ መቀበል አስፈላጊ ነው። ተስፋችን ግን ፈጽሞ ሊያልቅ አይገባውም
"We must accept finite disappointment, but never lose infinite hope."
Your browser doesn’t support HTML5