አንዲትም ሲጃራ ብትሆን ማጨስ... ያው... ማጨስ ነው

A woman smokes a cigarette in Washington, D.C.

በአዲሱ የጤና ምርምር መሰረት በብዛትም ሆነ በትንሹ ማጨስ የሚያመጣው የጤና እክል ተመሳሳይ ሆኗል። በቀን አንድም ሲጃራ ማጨስ ቢሆን የህይወት ዘመንን ያሳጥራል ነው የሚለው በቅርቡ የተደረገው ጥናት ውጤት። ማጨስን በማቆም ግን እድሜን ማራዘም ይቻላል።

ለአስርተ አመታት የተደረገው ይህ ጥናት የሲጃራን አደገኛነት አረጋግጧል። አንዳንድ ሰዎች በቀን የተወሰነ ምናልባትም አስር ወይም ከዛ ያነሰ ሲጃራን ማጨስ በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በጣም አነአስተኛ እንደሆነ በመገመት በሲጃራ ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎች እንደ ሳምባ ካንሰርና ከልብ ጋር ከተያያዙ ህመመሞች የሚይዟቸው አይመስላቸውም።

Your browser doesn’t support HTML5

አንዲትም ሲጃራ ብትሆን ማጨስ... ያው... ማጨስ ነው