በሊብያ ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ የሚኒስትሮች ስብሰባ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ

የአኅጉራዊና የሰሜን አፍሪቃን አከባቢ ፀጥታ ለማረጋገጥ በሊብያ ሰላም መስፈን እንዳለበት መሪዎች ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን ዛሬ በሚጠናቀቀው የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ሰባኛ ጉባኤ በሊብያ ላይ በማተኮር ከሚኒስተሮችና ከከፍተኛ የዓለም አቀፍ መሪዎች ጋር በሊብያ ሰላምና ጸጥታ ላይ የጎን ስብሰባ አካሄደዋል።

በትናንትናው እለት አርብ ፣ በአውሮፓ አቆጣጠር መስከረም 2015 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ የተካሄደው ውይይት ሰላም በሊብያ እንዲሰፍን ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን ለዓለም መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የወደፊት መሪዎችና የሕዝብ ወኪሎች በበኩላቸው ሕዝቡን በሚያሳትፍ ሁኔታና ፖለቲካዊ ውህደት የማምራት እድል ለመፍጠር መጣር አለባቸው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ

ስብሰባው በአኅጉራዊና በሰሜን አፍሪቃ አከባቢ ጸጥታና ሰላም ለማስፈን ያለመ ሲሆን፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአፍሪቃ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት የሊብያ ግብጽ ሱዳን ናይጄርያና ሌሎች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ወኪሎችን አሳትፏል።

በአሁኑ ጊዜ በሊብያና በአከባቢዋ ያለውን ቀውስ በብቸኛ አገር መሪነት ወይም በጦር ሃይል መፈታት እንደማይገባው ተሳታፊዎቹ ተቃውሞዎቻቸውን ገልፀዋል።

በማስቀጠል፣ ዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ በሊብያ ፖለቲካዊ መስመር ለማስፈን የሚቻለው ሕግና ሰብዓዊ መብቶች መጀመሪያ መከበር እንዳለባቸው የዓለም አቀፍ መሪዎች ተስማምተዋል።

በዚ አጋጣሚ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ “የሊብያን መሪዎች፣ በተለይ ዛሬ ከኛ ጋር ተሰብስበው የሚገኙት ወኪሎች፣ የሊብያ ሕዝብን ስቃይና መከራ ለማቆም ባንድ መንፈስ መስማማት አለባቸው። የወደፊት መሪዎችና የሕዝብ ወኪሎች በበኩላቸው ሕዝቡን በሚያሳትፍ ሁኔታና ፖለቲካዊ ውህደት የማምራት እድል ለመፍጠ መጣር አለባቸው” ብለዋል።

የስብሰባው ተሳታፊዎች የሽብር ቡድኑን አይሲስ በዓለም ደረጃና በሊብያ እየጠነከረ እንዳይሄድ ሥጋታቸውን ገልጸው፣ የፍልሰተኞችና የሰደተኞችን ቀውስ፣ የሊብያን ቁጠባና ሌሎች የጸጥታ ጉዳዮች በማንሳት ተወያይተዋል። ተሳታፊዎቹ በሊብያ ተደራጅቶ የሚሰራውን የተባበሩት መንገስታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤትን ስራ ወይም(UNSMIL)ን በመደገፍ ስብሰባውን አጠናቀዋል።

በሊብያ ያተኮረ የዓለም አቀፍ ሚኒስተሮች ስብሰባ