በጎንደር ከተማ ትላንት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሦስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነገረ

ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር

Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደር ከተማ ትላንት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሦስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነገረ

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ትላንት ደርሷል በተባለው የተኩስ ልውውጥ በሁለት ቤተ እምነቶች ላይ በደረሰው ጥቃት 2 ሰዎች ሲሞቱ 3 ሰዎች መቁሰላቸውን በኢትዮጵያ የኦርቶዶህ ተዋህዶ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ህሩይ አባ ዮሴፍ ደስታ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት በከተማው ዙሪያ እና በከተማው ውስጥ በሚገኙ አማንኤል እና ፈለገህይወት ቤዛዊት ማርያም በተባሉ ቤተ ክርስቲያኖች አንድ አገልጋይና አንድ ተማሪ መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡

SEE ALSO: በሰሜን ጎንደር ግጭት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ

የፈለገ ህይወትቤዛዊት ማሪያም አስተዳዳሪ መሆናቸውን የነገሩን መልዓከ ህይወት መምህር ዐቢይ ዘላለም እንደተናገሩት በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ገብተው አንድ አገልጋይ ተኩሰው መግደላቸው እና ሌላ አብሮት የነበረ ተማሪን ማቁሰላቸውን ነግረውናል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ከሰዓት በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ በትናንትናው ዕለት መስከረም 7/2017 ዓ/ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉ የትራንስፖርት አገልገሎት እና የንግድ ተቋማት አገልግሎት ዛሬ መስከረም 8/2017 ዓ.ም በከተማው በሁሉም አካባቢዎች በተሟላ ሁኔታ መጀመሩን ገልፆል፡፡ ስጋት ገብቶናል ያሉ ነዋሪዎች ግን አሁንም ከቤት መውጣት አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡