በኮንሶ የሕዝብ ተወካይ 14 ሰው ሞተ ሲሉ የክልሉ መንግሥት 6 ነው ይላል

  • መለስካቸው አምሃ

ፋይል- ኮንሶ

ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን በጥቃቱም ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሕይወት መጥፋቱን፤ በዞኑ ፖሊስ ጣቢያም የዐስራ አራት ሰው አስክሬን እንደሚገኝ እንደተናገራቸው ገልጸው በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ወደ 1000 ሺህ የሚጠጉ አባወራዎች ቀያቸውን ጥለው መጥፋታቸውን በሕዝብ እንደተመረጡ ከሚነገረው የኮሚቴ አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንሴ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። እሳቸው በተጨማሪ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የደቡብ ክልል መንግሥት ነው ይላሉ።

የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸው በኮንሶ በተቀሰቀሰ ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን ገልጸው ለጥፋቱ ተጠያቂዎች ግን የሕዝብ ወኪል ነን የሚሉ ሽፍቶች ናቸው ሲሉ ከሰዋል። በአሁኑ ሰዓትም ሁኔታው መረጋጋቱን ጨምረው አስረድተዋል።

ከሕዝብ እንደተወከሉ ከሚናገሩት የኮሚቴው አባል አንዱ የሆኑት አቶ ገመቹ ገንሴ ተኩሱ እንደቀጠለ መሆኑን ይናገራሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኮንሶ የሕዝብ ተወካይ 14 ሰው ሞተ ሲሉ የክልሉ መንግሥት 6 ነው ይላል