የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በብራስልስ ጥቃት ለሞቱና ለተጎዱ ሰዎች ሃዘናቸውን ገልጸዋል

  • ሰሎሞን ክፍሌ
አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን፥ በብራሰልሱ የሽብር ጥቃት ከተገደሉት ከ 30 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች መካከል ሁለቱ አሜሪካውያን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ (John Kerry) ዛሬ በብራሰልስ ከቤልጂግና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ጋር ተገናኝተው፥ በማክሰኞው የአሸባሪዎች ጥቃት ለሞቱና ለተጎዱ ሰዎች ሁሉ ሃገራቸው የተሰማትን ሃዘን ገልጸዋል።

አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን፥ በብራሰልሱ የሽብር ጥቃት ከተገደሉት ከ 30 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች መካከል ሁለቱ አሜሪካውያን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አሁን የደረሰው ጥቃት ዓላማችንን አያስቀይርም። ይልቅስ በተጠናከረ ሃይል ተመልሰን ይህን አጉል እምነታችሁን እና ፈሪ አስተሳሰባችሁን ከምድረ-ገጽ እስክናጠፋ እረፍት አይኖረንም።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ

ጆን ኬሪ የጥቃቱ ሰለባ ስለሆኑት አሜሪካውያን ዝርዝር መግለጫ ባይሰጡም፥ አንደኛዋ መምህርት ግን የፋሲካን በዓል ከቤተሰባቸው ጋር ለማክበር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እየተመለሱ ነበር ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስና የህብረቱ አባል ሃገሮች የዋህ ሲቪሎችን ለሚገድሉና ለሚያቆስሉ ሁሉ መልዕክት አላቸው ሲሉም ተናግረዋል ጆን ኬሪ ”አሁን የደረሰው ጥቃት ዓላማችንን አያስቀይርም። ይልቅስ በተጠናከረ ሃይል ተመልሰን ይህን አጉል እምነታችሁን እና ፈሪ አስተሳሰባችሁን ከምድረ-ገጽ እስክናጠፋ እረፍት አይኖረንም።” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከቤልጂጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቻርልስ (Charles Michel) ጋር ተገናኝተው የተወያዩት በጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። የቤልጂጉ መሪ በዚሁ ወቅት ሲናገሩ፥ ወደፊት ሌላ የሽብር ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል ከዩናይትድ ስቴትስና ከአውሮፓ ህብረት ሀገሮች ጋር በቻልኩት አቅም ሁሉ ተባብሬ እሠራለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል።

የብራስልሱ የቦምብ ጥቃት መታሰብያ