ኢንተርፖል በሕገወጥ መንገድ ፍልሰተኞችን የሚያሸጋግሩትን 11 ወንጀለኞች ለመያዝ በሚያደርገው ጥረት ሕዝብ እንዲሳተፍ ዛሬ ጥሪ አስተላለፈ።
ዋሽንግተን —
ዋና ጽሕፈት ቤቱ ፈረንሳይ የሆነው ዓለምአቀፉ የፖሊስ ድርጅት(ኢንተርፖል) እስካሁን በበርካታ ሃገሮች ውስጥ 26 በሕገወጥ መንገድ ፍልሰተኞችን በማሸጋገር እጃቸው አለበት ተብለው የሚከሰሱ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ገልጿል።
ለኢንተርፖል የአደን ዘመቻ ድጋፍ ሰጪ ክፍሉን በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት ሚካኤል ኦኮነል ስለዚሁ ሲናገሩ “ወንጀለኛው መረብ ሕገወጥ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሰዎች ደህንነት ምንም ደንታ ስለሌለውና እንደ ማንኛውም ግዑዝ የንግድ ሸቀጥ ስለሚቆጥራቸው፥ በዓለም ዙሪያ ለደረሰው ሰቅጣጭ አደጋ መጋለጣቸውን ተገንዝበናል” ብለዋል።
ኦፐርሬሽን ሃይድራ የተሰኘው ይህ የኢንተርፖል ዘመቻ ዓላማ፥ መድረሻ አጥተው ተስፋ በቆረጡ ስደተኞች ዝውውር ማትረፍ የሚፈልጉትን የእነዚህን ወንጀለኞች መረብ መበጣጠስ እና ግለሰቦቹን እያደኑ ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ሲሆን፥ መረጃ ያለውን ማንኛውንም ሰው ደግሞ እንዲጠቁም ማበረታታት ነው።
በዚሁ መሠረት ኢንተርፖል በዛሬው ዕለት ከተጠርጣሪዎቹ የ11ዱን ምስል በድረገጹ አውጥቷል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5