በጎንደር ከተማ በተቀሰቀው ግጭት ንብረታችን ወደመብን ካሉ ግለሰቦች ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ

Britaniya - Kral ailəsi Milad Günü mərasimində müqəddəs Mari Maqdalina kilsəsində<br /> <br /> <br /> <br /> &nbsp;

ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀው ቀውስና ብጥብጥ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን መንግስትና የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።

በርካታ ሆቴሎችን ጨምሮ ትክክለኛ መጠኑ ለጊዜው ያልታወቀ ንብረት እንደወደመና እንደተዘረፈ ንብረታችን ወደመብን ያሉ ግለሰቦች ይናገራሉ።

አቶ ተስፋይ በላይ የተባሉ የባህረ-ሰላም ሆቴል ባለቤት ሆቴላቸው መውደሙንና በውስጡ የነበረው ንብረት መዘረፉን የመኖሪያ ቤታቸውም በተመሳሳይ በኃይል ተሰብሮ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መዘርፉን ይናገራሉ። የቤተሰባቸውን አባላት የሚያሳርፉበት መጠለያ ማጣታቸውን አመልክተዋል።

ወ/ሮ ሸዊት አባዲ የተባሉ በሶስት ፈረቃ 115 ሰራተኞችን ቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሆቴል ባለቤት በበኩላቸው የሆቴል ቤታቸው መስተዋት መሰባበሩንና በንብረት ላይም ላይ ጉዳት መድረሱን ይናገራሉ።

በሌላ በኩል በቅርቡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋግራቸው “የወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ አቶ አደራጀው ዋኜ በጎንደር ከተማ ንብረታቸው የወደመባቸው የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውንና በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ላይ እንቅፋት የፈጠሩ ናቸው” ማለታቸው ተዘግቧል። አንዳንዶቹ ለገዢው ፓርቲ የሚሰልሉ ናቸው ብለዋል።

“ንብረት እንደወደመባቸው ካስታወቁ ወገኖች የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሁለቱ ግን “ፈጽሞ” ሲሉ ያስተባብላሉ።

የአሜሪካ ድምፅ ወደ ጎንደር እና ሁማራ ስልክ በመደወል ወ/ሮ ሸዊትን እና አቶ ተስፋዬን አነጋግሯል።ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀው ግጭት ንብረታችን ወደመብን ካሉ ግለሰቦች ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ