በጋምቤላ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ ምሽት በጀመረውና በማግስቱ ሰኞም በቀጠለው ግጭት፣ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የክልላዊ መንግሥቱ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ፣ በግጭቱ ሁለት ሰዎች መገደላቸውንና አራት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
በጋምቤላ ከተማ ግጭት ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ
በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ እና የሪፈራል ሆስፒታሎችም፣ በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎችን እያከሙ እንደሚገኙና የሞቱም መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።