በፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በተጀመረው የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች መርሐ-ግብር፣ 14 የደቡብ ሱዳን ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገለጠ።
ተመራጮቹ ወጣቶች በቀጣዩ ሳምንት ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ይጀምራሉም ተብሏል። ከዚያም በተለያዩ እንደ ንግድ አስተዳደር፣ ሲቪክ አመራርና ሕዝባዊ አስተዳደር ለመሰሉ ስልጠናዎች ወደ አሜሪካ ዩኒቨርሲቲና ወደ ሌሎችም ኮሌጆች ይላካሉ።
አሥራ-አራቱ የደቡብ ሱዳን ወጣቶች፣ ከሌሎች የአፍሪቃ አገሮች ከሚውጣጡ ወደ 1,000 ያህል ወጣቶች ጋር ተደባልቀው የስልጠናው መርሓ-ግብር ተካፋዮች እንደሚሆኑም ታውቋል።
ጁባ የሚገኘው የየዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የመረጃ ዳይሬክተር ክሪስ ማዴ እንደገለጹት፣ ሰባቱ ወንዶችና ሰባቱ ሴቶች የተመረጡት፣ ከ400 ተወዳዳሪዎች መካከል ነው።
የሁሉም አመልካቾች ዕድሜ ከ25-35 ዓመት መሆኑን የገለጹት ማዴ ከዚህ ቀደም ማናቸውም ዩናይትድ ስቴትስ መጥተው የማያውቁ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።
ከዚህ በፊት በወጣቶች መርሐ-ግብር ላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈው ነበር። ያነጋገርናቸውን ወጣቶች ቪድዮዎች ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ከያሊ ምን ተማራችሁ? ወጣት ኢትዮጵያዊያንንስ እንዴት ይረዳል?
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5