በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
ቃጠሎው መድረሱን ያረጋገጡት የዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ በሕይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ቃጠሎው ዳመራ በሚባለው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የተማሪዎች ማደሪያ ላይ የተነሣው ትናንት፤ ማክሰኞ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ እንደነበረ ተማሪዎቹ ተናግረዋል።
በእሳቱ አርባ የማደሪያ ክፍሎች ያሉባቸው በቆርቆሮ የተሠሩ አራት ምድቦች ወይም ብሎኮች መቃጠላቸውንና ንብረቶቻቸው መውደማቸውን ተማሪዎቹ ጠቁመዋል።
የዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ደኅንነት ዳይሬክተር ኮማንደር እሸቱ ከበደ ስለቃጠሎው፤ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ፤ ለማጥፋት ስለተወሰደው እርምጃ ሲናገሩ ለማጥፋት ተማሪዎቹ መረባረባቸውን፣ እሳቱ ሲነሳ ተማሪዎቹ ማንበቢያ አካባቢ የነበሩ በመሆኑ በማንም ላይ ጉዳት አለመድረሱን አመልክተዋል።
ስለቃጠሎው ምርመራው መቀጠሉን ኮማንደር እሸቱ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ እሳት አጥፊዎች የደረሱት ዘግይተው አራቱ ብሎኮች ከተቃጠሉ በኋላ መሆኑን ተማሪዎቹ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5