"ለሶማሊያ የውጭ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ኃላፊ ብቸኛ አካል የሀገሪቱ መንግሥት ነው"-ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ

  • እስክንድር ፍሬው

ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ

የጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መሪዎች ወደ አዲሰ አበባ ሲመጡ የቆዩት በሀገሪቱ የፌደራል መንግሥት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

የጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መሪዎች ወደ አዲሰ አበባ ሲመጡ የቆዩት በሀገሪቱ የፌደራል መንግሥት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱን የውጭ ዲፕሎማሲ ግንኙነት በተመለከተ ኃላፊነት ያለበት ብቸኛ አካል የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ነው ብለዋል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፡፡

ከፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ ጋር ሰሞኑን በብሔራዊ ቤተመንግሥት በሰጡት መግለጫ ነው ጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪም ደሣለኝ ሰለ ጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መንግሥታት የተናገሩት፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

"ለሶማሊያ የውጭ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ኃላፊ ብቸኛ አካል የሀገሪቱ መንግሥት ነው"-ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ