የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ሳምንት ቦሶማሌላንድ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወደሰ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ “’ምርጫው በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መንገድ’ በመካሄዱ ኢትዮጵያ የሶማሌላንድን ሕዝብ እንኳን ደስ አለህ ትላለች” ብሏል። መግለጫው በተጨማሪም “ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ” በማካሄዱ ለሶማሌላንድን ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ያለውን አድናቆት ገልጧል።
"ይህ ሂደት የሶማሌላንድን አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት የሚያንፀባርቅ ነው" ሲልም አክሏል።
የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ጠንካራ ግንኙነት ለዓመታት የዘለቀ ሲሆን፤ እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባህር ዳርቻ በሊዝ መከራየት የሚያስችል እና በምላሹ ለሶማሌላንድ ሉአላዊ እውቅና የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የሃርጌሳ ባለስልጣናት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና ሶማሌላንድን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትመለከተው ሶማሊያ ‘ሉዓላዊነቴን ጥሷል’ ስትል በሁለቱ እገኖች የተፈረመውን ስምምነት አውግዛለች። ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በበኩላቸው ስምምነቱን ‘ትክክለኛ ነው’ ሲሉ ይከላከላሉ።
የሶማሌላንዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ጉሌይድ አህመድ ጃማ በሰጡት አስተያየት እንደጠቆሙት፤ የወቅቱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በምርጫው ካሸነፉ የመግባቢያ ሰነዱን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ቅሬታ እንዳላቸው የገለጡ
ተቃዋሚ ቡድኖችም በበኩላቸው ስምምነቱን መቀበላቸው ተመልክቷል።