በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ገለጸች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ

ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋራ የተደረገውን የመግባቢያ ስምምት በተመለከተ፣ በማኅበራዊ የመገናኛ አማራጮች የሐሰት መረጃዎች እየተሰራጩ ናቸው፤ ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡

SEE ALSO: ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የባሕር በር ውል ቋጠሩ
ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነቱን ለመሰረዝ እንደወሰነች”

“ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነቱን ለመሰረዝ እንደወሰነች” የሚገልጽ ይዘት ያለው መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ፣ ትላንት ረቡዕ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ፣ የመግባቢያ ስምምነቱ የሚገኝበትን ደረጃ በተመለከተ “ወቅቱ ሲደርስ ይገለጻል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ቃል አቀባዩ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ግዛት ጥሰው እንደገቡ፣ በሶማሊያ በኩል የቀረበውን ክስም “ሐሰት ነው” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ገለጸች