የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ፣

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

በያዝነው ሳምንት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንካራ ላይ የተፈጸመውን ስምምነት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ኢጋድ በመልካም ተቀብለውታል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ወገኖች አንዱ የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዐላዊነት ያከብራል። በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኝት ጥያቄ በተመለከተ በጋራ እንደሚሠሩበት ተመልክቷል። በሌላ በኩል የአንካራው ስምምነት፣ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚኾን አላመላከተም።

ሃሩን ማሩፍ ስምምነቱ በሁለቱም ሃገራት እንዲሁም ከሶማሊላንድ ጋራ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ላይ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ ሁለት ተንታኞችን አነጋግሯል። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።