በኢትዮጵያ ኣፈር በማይጠቀም እርሻ በተለይም የእንስሳት መኖ ማምረት የሚቻልበትን ዘዴ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
መቀሌ —
ይህን ዘዴ ያስጀመረው YB የእፅዋት ማይክሮ ፕሮፓጌሽን የተባለ ድርጅት ሲሆን ምርቱ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በድርቅ ምክንያት ለተጐዱ የኢትዮጵያ ኣከባቢዎች እንደ ኣንድ ጥሩ ኣማራጭ ሆኖ ቀርቧል።
የድርጅቱ መስራችና ስራ ኣስከያጅ በሐይሉ ኣብርሃ ዘዴው ኣፈር ኣይጠቀምም፣ ብዙ ውሃ ኣይጠይቅም፣ በትንሽ ቦታ ብዙ ምርት ማግጀት ይቻላል፣ በአንድ ቦታ ተወስኖ የሚሰራ እርሻ ሳይሆን ገበሬው ወዳለበት ቦታ በመቅረብ የሚዘጋጅ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል ብሏል።
በ50 ሜትር ስኵር መሬት 6 ኩንታል ምርት ማግኸት እንደሚቻል የገለፀው በሐይሉ የእድገቱም ጊዜ ከነበረው በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚደርስ ይናገራል። በዚሁም መሰረት በ90 ቀናት ይበቅል የነበረው ሳር በዚሁ ዘዴ በ7 ቀናት ውስጥ ማድረስ ይቻላል።
በተለይም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ላጋጠመው ድርቅ በተለይም እንስሳት በመኖ እጥረት እየተጐዱ ባለበት ሁኔታ ላይ የተሻለ ኣማራጭ ሆኖ ቀርቧል ብላል ተመራማሪው።
ዘገባውን ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5