ኦሮሚያ ዛሬ ግድያና የተቃውሞ ሰልፍ ማስተናገዷን ነዋሪዎችና የክልል ባለሥልጣናት ተናገሩ

ነቀምት ከተማ የተካሄደ ሰልፍ

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሐዊ ጉዲና ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ውስጥ የሶማሌ ክልል የታጠቁ ኃይሎች ገብተው ከ80 በላይ የአርሶ አደር ቤቶች ማቃጠላቸውንና እስካሁን ቦታውን ተቆጣጥረው መያዛቸውን የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ተናገሩ። በሌላ በኩል ጋዱሎ በተባለ ቀበሌ ላይ በዚህ የተበሳጩ የሟች ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ሶማሌዎችን ማጥቃታቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮሚያ ዛሬ ግድያና የተቃውሞ ሰልፍ ማስተናገዷን ነዋሪዎችና የክልል ባለሥልጣናት ተናገሩ

እስካሁን ሁለት ሰው ሞቶ ሁለት ሰው መቁሰሉን ተናገረው የመብራትና የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ መረጃ ለማግኘት ተቸግረናል ብለዋል። በሁኔታዎች ግራ ተጋብተናል ያሉት የዞኑ ኃላፊ በዚህ ሳምንት ብቻ ከዚህ አደጋ ውጪ በዞኑ ስድስት ሰው ተገሎ አምስት ቆስሏል ብለዋል።

የሶማሌ ክልልን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ስልካቸው ባለመነሳቱና ተነስቶም በመዘጋቱ ማካተት አልተቻለንም። በሌላ በኩል በምዕራብ ወለጋና በምስራቅ ወለጋ የሚገኙ ነዋሪዎች “ግድያ ይቁም መከላከያ ከሕዝብ ቆን ይቁም” የሚል መልዕክት ያዘለ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገርዋል።