እ.አ.አ በ2020 ቫይረሱን ከአለማችን ጨርሶ የማጥፋት አለም አቀፍ እቅድ በኢትዮጵያ ምን ያህል እንደተተገበረ በመገምገምና ለቀጣይ አመታትም ምን ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንዳለበት በመመካከር ነበር ቀኑ ታስቦ የዋለው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የፌደራል የኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኖ በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ስርጭትና መከላለልን በተመለከተ ካለፈው አመት ጋር በማነፃፀር የተሻለ ለውጥ እንደታየ ገልፀዋል።
የብሔራዊ የኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያና መከላከያ ፅ/ቤት የእቅድ ክትትልና ግምገማ ኦፊሰር ዶ/ር አቻምየለህ አለባቸው በኢትዮጵያ በቫይረሱ የሚሞተው የሰው ቁጥር መቀነስ ከፍተኛ ቢሆንም አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመቀነስ ዙሪያ አሁንም መስራት ይገባናል በማለት ይናገራሉ።
ከመስታወት አራጋው ጋር ያደርረጉትን ቆይታ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5