ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ተገለፀ

  • ቪኦኤ ዜና

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ፤ የመጀመሪያቸው ለኾነ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ካይሮ ላይ ከሱዳን መሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።

የአፍሪካ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት በያዝነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ያለመውጣታቸው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እንዳይተገበር እንቅፋት ከሆኑ ምክኒያቶች አንዱ ነው ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።