በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች የሽምግልና ጥረት በካይሮ


የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች የሽምግልና ጥረት በካይሮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች የሽምግልና ጥረት በካይሮ

የስድስቱ የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች፣ በግብጽ አስተናጋጅነት፣ ዛሬ ኀሙስ ካይሮ ላይ ተሰብስበው፣ ውጊያው ስለሚገታበት መንገድ መክረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ፡- የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የቻድ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የሊቢያ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የሁለቱ ወገኖች ውጊያ፣ ወደተራዘመ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀየር ለመከላከል ብሎም እየተባባሰ ለቀጠለው ሰብአዊ ቀውስ መፍትሔ ለመሻት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከታታይ ጥረቶች ተካሒደዋል፡፡ ዛሬ፣ የሱዳን አጎራባቾች መሪዎች የተገናኙበት መድረክ፣ የግብጹ መሪ የጀመሩት ዐዲስ የሰላም ሽምግልና ሙከራ ነው፡፡

በሮይተርስ እና በአሶሺዬትድ ፕሬስ የተጠናቀሩ ዘገባዎችን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG