ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ወኪል ፈረደሪካ ሞግሪኒ (Federica Mogherini) ወደ ኢትዮጲያ በመሄድ የአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጲያን ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ ለማክበር በአዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። ፈረደሪካ ሞግሪኒ በጉብኝታቸው፣ ከጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ከአፍሪቃ ሕብረት ሊቀወንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪቃ ጋር ያለውን ግንኙነት በተከያዩ መስኮች ማዳበር እንደሚችል አስታውቀዋል። በተለይም በኢኮኖሚ፣ መዋእለ ንዋይ፣ የዓለምአቀፉ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ እና ከአፍሪቃ ወደ አውሮፓ የሚያመሩ ፍልሰተኞችን በሚመለከት በንግግራቸው ላይ አንስተው ሃሳባቸውን ገልጸዋል። እነዚህን ጉዳዮች ሕብረቱ ከአፍሪቃ ጋር በመስራት ለማሻሻል እንደሚጥርም አስታውቀዋል። ሴቶችን በማስልጠና እና የስራ እድሎችን መፍጠርን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ ሞግሪኒ።
“እንደ ወጣት አውሮፓዊ ይህ አዲስ ትውልድ በአፍሪቃ ላይ ያለው አስተያየት ካለፈው የቀኝ ግዛት ታሪክ ነጻ የሆነ መጪውን በተግባራዊና ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ መመልከት የሚፈል ነው። የናንተ ወጣቶች ብርታታችሁ እንደሆኑ የኛም እንደዛ ናቸው። በተጨማሪም ሴቶቻችሁ ብርታታችሁ እንደሆኑ በአውሮፓ የሚገኙ ሴቶችም ብርታታችን ናቸው። ይህን ደግሞ የሴቶችን መብት በአፍሪቃ እድገት ማእከል እንዲገኝ ባደረጉት ዋና ጸሓፊ ዙማ ፊት ስናገር ትልቅ ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል።
ይህንን ለመደገፍ ሞግሪኒ ከጎበኙት ቦታ አንዱ፣ የራስ አደር ሴቶች ድርጅት(ራሴድ) ይባላል። ራሴድ የበጎ አድራጎት ድርጀት ሲሆን፣ በዝቅተኛ-ገቢ ያሉ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። የድርጅቱ ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌ ድረጅቱ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን ብዙ ሴቶችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የድርጅቱ ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌ ለየአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጲያ ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ ለማክበር በሂልተን ሆቴል የኮክቴል ግብዣ በተደረገበት አጋጣሚ እንደተገኙ ከገለጹ በኋላ፣ በተለያዩ ርእሶች ላይ ተወያይተው መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል። የፍልሰተኞች ጉዳይ ከርእሶቹ አንዱ መሆኑንም አስረድተዋል። የአውሮፓ ሕብረት ዝርዝር ስለጉባኤው በዌብሳይታቸው ላይ አቅርበዋል። ይህንን ፋይል በመጫን ይጎብኙ።
ሳሌም ሰለሞን የራስ አደር ሴቶች ድርጅት (ራሴድ) ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌን አነጋግራ ያቀረበችውን ዝርዝር ከተያያዘው ይድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ንግግራቸው እንዳበቃ ሞግሪኒ በቦታው ተገኝተው ከነበሩት የዓለምአቀፉ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ-ምልልስ አካሄደው ነበር።
"ኤርትራን በተመለከተ ሀገሪቱውስጥ በአንድ በኩል የሰብዓዊ መብቶች ሬኮርድ፥ በሌላ ወገን ደግሞ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል አስፈላጊ መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም" ብለው መልስ ሰጥተዋል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ። ሞግሪኒ ኤርትራ የውስጥ ችግሮቿን እንድታሻሽልም ጥሪ አቅርበዋል።ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የቪድዮ ፋይል ይመልከቱ።
Your browser doesn’t support HTML5
ከዚህ በፊትም ኤርትራ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል ጥረት እያደረገች መሆንዋን ዘግበን ነበር።