የሚጠጣ ወኃ እጥረት ኤሊ ዳር እና ገዋኔ ዞኖች ውስጥ በአፋር ክልል
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት ወዲህ በመጠኑና አስከፊነቱ ታይቶ የማይታወቀው ድርቅ፤ በአፋር ክልል በእንስሳትና በሰዎች ህይወት ላይ ያሳደረው ጫና ከባድ ነው። በድርቁ በተጠቁ ሌሎች አካባቢዎችም ወደ ሰማንያ ከመቶ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የእርዳታ ሰራተኞች አስታውቀዋል። በአፋር ኤሊዳርና ገዋኔ ወረዳዎች ከብቶች በግጦሽና ውኃ እጥረት ሞተዋል፤ የተረፉት ደግሞ ሰውነታቸው መንምኖና በበሽታ ተጠቅተው ይታያሉ።