በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ግጥሚያ ቀጥሏል

ቶሮንቶ-ካናዳ ላይ ሰላሣ ሦስተኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፈዴሬሽን የሦስተኛ ቀን ጨዋታዎቹን እያካሄደ ነው።

ESFNA in Toronto

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ግጥሚያ ቀጥሏል

ቶሮንቶ-ካናዳ ላይ ሰላሣ ሦስተኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፈዴሬሽን የሦስተኛ ቀን ጨዋታዎቹን እያካሄደ ነው።

በትናንት - ሰኞ ውሎ ስምንት ግጥሚያዎች ተካሂደዋል፤ በተለይ አትላንታና ዲሲ ስታር ያካሄዱት ስድስተኛው ውድድር፤ ኤትል ባሮና ሳን ፍራንሲስኮ ያካሂዱት የመጨረሻ ግጥሚያ ከበድ ያሉና ጥሩ ፉክክር የታየባቸው ነበሩ፡፡

የእግር ኳስ ግጥሚያዎቹን ከሚመሩት መካከል የፊፋ ዕውቅና ያላት ወጣቷ ሴት ዳኛ ትርሃስ ገብረዮሃንስ ትገኛለች፡፡

በነገው ምሽት - ማክሰኞ ደግሞ ለአንጋፋው የአካል ብቃት ባለሙያ ለግርማ ቸሩ የቶሮንቶ ማኅበረሰብ ዕውቅና እንደሚሰጥና እንደሚያከብረው ተገልጿል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡