ከፓሪስ ወደ ካይሮ ያመራ የነበረ የግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከሰከሰ

  • ቪኦኤ ዜና
አራት ሰዓት በሚወስደው በረራ ዛሬ ሓሙስ ግብፅ አየር ክልል እንደገባ ከበረራ መቆጣጠሪያ ራዳር የተሰወረውን አውሮፕላን ስብርባሪ ለማግኘት በሜዲቴራኒያን ባህር ፍለጋ ቀጥሏል።

ስድሳ ስድስት ሰዎች ይዞ ከፓሪስ ወደ ካይሮ በመብረር ላይ የነበረው የግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰው ኬቴክኒካዊ ብልሽት ይልቅ በሽብርተኝ ጥቃት ይመስላል ሲሉ የግብፅ የአቪየሺን ሚኒስትር ተናገሩ ።

የግብፅ የአቪየሺን ሚኒስትር

አራት ሰዓት በሚወስደው በረራ ዛሬ ሓሙስ ግብፅ አየር ክልል እንደገባ ከበረራ መቆጣጠሪያ ራዳር የተሰወረውን አውሮፕላን ስብርባሪ ለማግኘት በሜዲቴራኒያን ባህር ፍለጋ ቀጥሏል።

አደጋው እንደደረሰ ከግሪክ የወጡ ዘገባዎች እንዳሉት ከሆነ ከአየር የአውሮፕላኑ ስብርባሪ ነው ተብሎ የተጠረጠረ አካል ሳይታይ አልቀረም።

ከፓሪስ ወደ ካይሮ ያመራ የነበረ  የግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከሰከሰ

ዩናይትድ ስቴትስ ፒ 3 ኦሪዮን የሚባሉት የረጅም ርቀት ተጉዋዥ አውሮፕላኖች በመስጠት በፍለጋው በመተባበር ላይ መሆኑዋ ታውቁዋል

የዩናይትድ ስቴትስ የውች ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ ለግብፅ አየር መንገዱ አውሮፕላን ተሳፋሪዎች ቤተሰቦች የሃዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ከፓሪስ ወደ ካይሮ ያመራ የነበረ የግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከሰከሰ

ሚስተር ኬሪ ዛሬ ብረሰልስ ውስጥ ከተካፈሉበት የኔቶ የሰሜን አትላንቲክ ሀገሮች ቃል ኪዳን ድርጅት የሚንስትሮች ስብሰባ በኋላ በሰጡት ቃል የአደጋው መነሾ የሽብር ተግባር ይሁን አይሁን በግምት መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።