ድሬደዋ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ሦስት ሰዎች ሞቱ

ድሬደዋ ከተማ ጎርፉ ካለፈበት የገበያ መንደሮች አንዱ(በተለምዶ አሸዋ ገበያ ተብሎ ይጠራል)

በድሬደዋ ከተማ እና በአጎራባች ምስራቅ ሐረርጌ ከተሞች በትናንትናው ዕለት የዘነበው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ሦስት ሰዎች ሞቱ፣ አንድ ሰው ቆሰለ። አንድ ባጃጅ እና ዩዲ መኪናም በጎርፉ ተወስዷል፡፡ ሳቢያን እየተባለ በሚጠራው ሰፈር የተገንባ ትልቅ ድልድይም ለሁለት ተከፍሏል። ጽዮን ግርማ የድሬደዋ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

በድሬደዋ ከተማ እና በአጎራባች ምስራቅ ሐረርጌ ከተሞች በዘነበ ዝናብ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የጎርፍ አደጋ ሦስት ሰው መሞቱን እና ሁለት ሰው መቁሰሉን የድሬደዋ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኑኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በጎርፍ አደጋው አንድ ባጃጅ እና ዩዲ መኪና መወሰዱንም ጨምረው ተናግረዋል። ጽዮን ግርማ አቶ ፍቃዱ በየነን ማምሻውን ደውላ ጠይቃቸው ነበር የተናገሩት በዘገባው ተካቷል።

በተያያዘም በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋ ሮቢት ከተማ ባለፈው ሳምንት የደረሰ የጎርፍ አደጋ ቁጥራቸው ከሦስት መቶ በሚበልጡ ቤቶች ነዋሪ በኾኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።ሚያዝያ ዐስራ አንድ ለሦስት ሰዓታት ያለማቋረጥ የጣለው ከባድ ዝናብ በአራት ቀበሌዎች ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ ታውቋል።

በዕለቱ የከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ጎርፉ በሆቴሎችና ሌሎችም ንግድ ቤቶች ከባድ ጉዳት መድረሱን፣ ጎርፉ በትምሕርት ቤቶች ገብቶ ብዛት ያላቸው የመማሪያ መጽሐፍት ማውደሙን ገልጸዋል። በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ግን የለም ብለዋል።

ወደከተማዋ የጤና ዘርፍ ኣካባቢ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት ቤቶቹ እስከሃምሳ ሴንቲሜትር በሚደርስ ከፍታ በመጥለቅለቁ በደረሰው ጉዳት በአሁኑ ወቅት ለነዋሪዎች የምግብ የውሃና የኣልባሳት ርዳታ እየተደረገ ነው። ለህጻናት የአልሚ ምግብ ርዳት እየተሰጠ መሆኑንም ገልጸውልናል።

አጠር ያለውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ድሬደዋ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ሦስት ሰዎች ሞቱ