ፓኪስታን የአፍጋኒስታንን የሰላም ሂደት ለማንሰራራት ስለሚቻልበት መንገድ የሚነጋገር የአራትዮሽ ድርድር በማስተናገድ ላይ ነች።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን፣ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የሚካፈሉበት ድርደር በፓኪስታን እየተካሄደ ነው። ፓኪስታን የአፍጋኒስታንን የሰላም ሂደት ለማንሰራራት ስለሚቻልበት መንገድ የሚነጋገር የአራትዮሽ ድርድር በማስተናገድ ላይ ነች ።
የፓኪስታን ጠቅላይ ምኒስትር ናዋዝ ሻሪፍ የውጭ ጉዳይ አማካሪ ሳርታዥ ኣዚዝ ውይይቱን በንግግር ከፍተዋል።
የዕርቀ ሰላሙ ሂደት ዋና ዓላማ ታሊባኖቹን ወደድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመጡ ማድረግና የፖለቲካ ግባቸውን ለማሳካት ሁከትን እንዳይጠቀሙ ማበረታቻ መስጠት ነው ብለዋል።
አፍርጋኒስታን ውስጥ ባለፈው አንድ ዓመት የታሊባን ዓመጽ እየተስፋፋ መምጣቱ ጦርነት በበጣጠቃት ሃገር የባሰ ደም መፋሰስና አለመረጋጋት ይመጣል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የዜና ዘገባችንን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5