ጄክ ሰለቨን ለባይደንና ሺ ስብሰባ ቻይና ናቸው

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ከቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ ጋር ቤጂንግ

የዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ከቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ ጋር ቤጂንግ

የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቨን በህዳር ወር ከሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት ለማስከን ትላንት ማክሰኞ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር በቤጂንግ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ጉብኝቱ ፕሬዝዳንት ባይደን በጥር ወር ስልጣን ከመልቀቃቸው በፊት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና በቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ መካከል ለሚደረገው የመጨረሻ የመሪዎች ጉባኤ መንገድ ለመክፈት ያለመ ነው።

ወደ ዝግ ስብሰባ ከመግባታቸው በፊት ዋንግ ዪ የቻይና- እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነቶች ለዓለም እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ እጅ ወደ መጠምዘዝ መዞሩን በመጥቀስ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጤናማ እና የተረጋጋ ግንኙነት እንደሚኖር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

SEE ALSO: ቤጂንግ ላይ የቻይና እና የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ይነጋገራሉ

ሰለቨን በበኩላቸው ሁለቱም ወገኖች በማያግባቧቸውና በማያግባቧቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ገልጸው ስምምነት እና አለመግባባቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መፍታቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጉብኝቱ አለምአቀፍና ክልላዊ ውጥረቶችን ጨምሮ ከዩክሬን ወረራ በኋላ በታየው የንግድ ውጥረት፣ በሰብአዊ መብት ጉዳዮች እና ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት በማስመልከት ላይ ያተኮረ ነው።