የታገቱት 247 ወጣቶች ጉዳይ እንዳሳሰበው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ

  • ቪኦኤ ዜና

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ እና አሌ ዞኖች ተነሥተው ለደን ምንጣሮ ወደ ሕዳሴ ግድብ እያመሩ በነበሩበት ወቅት፣ አማራ ክልል ላይ “በፋኖ ታጣቂዎች ታግተዋል” የተባሉ 247 ወጣቶች ጉዳይ እንዳሳሰበው፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።

Your browser doesn’t support HTML5

የታገቱት 247 ወጣቶች ጉዳይ እንዳሳሰበው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ቤተሰቦች፣ ወጣቶቹ የቀን ሠራተኛ መኾናቸውን ገልጸው ደኅንነታቸው እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ወጣቶቹን በጉዟቸው ላይ እንደያዛቸው ያመነው የፋኖ ታጣቂ ቡድን፣ “የመከላከያ ሠራዊት እና የሚሊሻ አባላት ናቸው፤” ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።