“መሠረት ያለው የማንነት ስሜት አይሰማቸውም። ምክኒያቱም ከሞሮኮያውያን ወይም ቱኒዝያዊያን፤ ሱዳናውያን አለያምም ሌላ ወገን ከሆኑ ወላጆቻቸው የሚወለዱ ሁለተኛና ሦሥተኛ ትውልድ ሊሆኑ ስለሚችሉ፤ የወላጆቻቸውን አገር ማንነት አይላበሱም፤ ወይም ራሳቸውን የዚያ የተወለዱና ያደጉበት ተቀባይ አገር አካል አድርገው አይቆጥሩም።"ቶም ሳንደርሰን የስትራተጂና የዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል ዲሬክተር
ዋሽንግተን ዲሲ —
በትላንትናው ዕለት በብራስልስ አውሮፕላን ጣቢያ የፈነዱትን ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ ፈንጂዎችና በከተማይቱ እምብርት ከሚገኝ የባቡር ጣቢያ የፈነዳውን አንድ ሌላ ቦምብ ጨምሮ እስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን (ISIL) ለሦሥቱ የቦምብ ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዷል።
Your browser doesn’t support HTML5
ፈንጂዎቹን ያፈነዱት ሁለቱ አጥፍቶ ጠፊዎች መንግስታዊው የቤልጂየም የዜና ማሰራጫ RTBF እንደዘገበው ካሊድ እና ብራሂም አል-ባክራዊ የተባሉት ሁለት ወንድማማቾች ከዚህ ቀደም በሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂ የነበሩ ቢሆንም፤ ከአሸባሪ ጋር የታወቀ የቀደመ ግንኙነት ግን አልነበራቸውም።
መሠረት ያለው የማንነት ስሜት አይሰማቸውም። ምክኒያቱም ከሞሮኮያውያን ወይም ቱኒዝያዊያን፤ ሱዳናውያን አለያምም ሌላ ወገን ከሆኑ ወላጆቻቸው የሚወለዱ ሁለተኛና ሦሥተኛ ትውልድ ሊሆኑ ስለሚችሉ፤ የወላጆቻቸውን አገር ማንነት አይላበሱም፤ ወይም ራሳቸውን የዚያ የተወለዱና ያደጉበት ተቀባይ አገር አካል አድርገው አይቆጥሩም። ስለሆነም፥ ሞሮኮዊነት ወይም ፈረንሳዊነት፤ ቱኒዝያዊነት አለያም ቤልጂያዊነት፤ ሱዳናዊነት ወይም ጣሊያናዊነት አይሰማቸውም።ቶም ሳንደርሰን የስትራተጂና የዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል ዲሬክተር
በጥቃቶቹ ሰላሳ አራት ሰዎች መገደላቸውና ከ200 በላይ መቁሰላቸው ተዘግቧል።
Your browser doesn’t support HTML5