ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች የሰጠችውን የጥገኝነት ፍቃድ አልቀለበሰችም

በዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ለመሳተፍ ወደ ቦትስዋና በቅርብ ለሄዱት 10 የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት የቦትስዋና መንግስት ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም በማለት በቦትስዋና ጥገነት የጠየቁት።

ትናትና የቦትስዋና ጋዜጣ መንግስቱ ሃሳቡን ቀይሯል በማለት ዘግቦ ነበር። ነገር ግን ዘገባው የተዛባ እንደሆነ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኘውን የኤርትራውያን የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት እንቅስቃሴ (EMDHR) ድርጅትን ወክለው በደብብ አፍሪቃ ውስጥ የሚኖሩት ኤርትራውያኑ ተሟጋች እያሱ ዓንደማርያም ሃብተማርያም ገልጸዋል። ከበደቡብ አፍሪቃ “የአፍሪቃ ሪቪው” ጋዜጠኛው ጋር በተደረገው ቃለ-ምልልስ ላይ የተዛባ መረጃ እንዴት ሊተላለፍ እንደቻለም ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል።

“እኔ መጀመርያ ላይ የነበረውን የጥገኝነት ጉዳይ የቦትስዋና መንግስት እንዴት እንደሚከታተለው ነበር ያካፈልኩት ። ጋዘጠኛው ግን መጀመሪያ ሲያነጋግረኝ በቅርብ እየተከታተልኩት የነበርኩ መስሎት ነበር። የመግባባት ችግር ነበር ። ነገሩ ግራ ከተጋባ እኔም በበኩሌ ጉድለት ካለኝ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ለመጠየቅ እፈልጋለው” ብለዋል።

የጥገኝነት አመልካቾቹ መጀመርያ የወሰዷቸው ወደ እስር ቤት ነበር። እስር ቤቱ በከፍተኛ የኤለኢትሪክ ሽቦ የታጠረ፣ ወንጀለኞች የሚጠበቁበት ስፍራ ነው። 24 ሰአት ሙሉ በካሜራ የሚጠበቅ ነው። አሁን ያሉበት ዱክዊ (Dukwi Refugee Camp) የስደተኞች ካምፕ ግን እንደሰፈራ ያለ ቦታ ነው። ያም ሆኖ ጥበቃ አይደረግበትም ማለት አይደለም።
ቦትስዋናዊ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ዲክ ቤይፎርድ

ቦትስዋናዊ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ዲክ ቤይፎርድ ጉዳዩ መምታታቱና መወዛገቡ የጀመረው ለመጀመርያ ግዜ እንዳልሆነ ካስታወቁ በኋላ፣ ስለ ጉዳዩ አስመልክተው "የጥገኝነት አመልካቾቹ መጀመርያ የወሰዷቸው ወደ እስር ቤት ነበር። እስር ቤቱ በከፍተኛ የኤለኢትሪክ ሽቦ የታጠረ፣ ወንጀለኞች የሚጠበቁበት ስፍራ ነው። 24 ሰአት ሙሉ በካሜራ የሚጠበቅ ነው። አሁን ያሉበት ዱክዊ (Dukwi Refugee Camp) የስደተኞች ካምፕ ግን እንደሰፈራ ያለ ቦታ ነው። ያም ሆኖ ጥበቃ አይደረግበትም ማለት አይደለም” ብለዋል።

በመቀጠልም የኤርትራውያኑ ጉዳይ ወደ ሦስተኛ አገር ለማሸጋገርና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥረት ላይ እንዳሉ ጠበቃው አስረድተዋል። የቦትስዋና መንስግስት የፍተህ የመከላከያና የጸጥታ ጥበቃ ሚንስትሩ የጥገኝነት ማመልከቻቸው እንዳልተቀለበሰ በመገናኛ ብዙሃን አረጋግጠዋ። በቦትስዋና የሚኖሩ ዶ/ር አዳነ ገብረመስቀል በበኩላቸው ለተጫዋቾቹ እየተሟገቱ ይገኛሉ።

“የቦትስዋና መንስግስት የፍተህ የመከላከያና የጸጥታ ጥበቃ ሚንስትሩ በቴሌቭዝን በሰጡት መግለጫ መሰረት ይህህንኑ፣ ማለትም የኤርትራውያኑ የጥገኝነት ማመልከቻ በቦትስዋና መንግስት ውድቅ አለመደረጉን ገልጸዋል ብለዋል። ወደ ሦስተኛ አገር ለማዘዋወር እንደሚጥሩም ተናግረዋል” ብለዋል።

ሳሌም ሰለሞን ቦትስዋናዊ ጠበቃቸውን ዲክ ቤፎርድንና ሁለት ኤርትራውያን ተሟጋቾች እያሱ ዓንደማርያም ሃብተማርያም እና ዶ/ር አዳነ ገብረመስቀል ጋር ተነጋግራለች። ኤርትራያኑ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኘውን የኤርትራውያን የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ተንቀሳቃሽ ድርጅት ወክለው በደብብ አፊሪቃና በቦትስዋና ሆነው ለተጫዋቾቹ ይሟገቱላቸዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች የሰጠችውን የጥገኝነት ፍቃድ አልቀለበሰችም