የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታና የመንግሥት ምላሽ

በአማራ ብሔራዊ ክልል የተቀነባበረ የማፍረስ ዘመቻ እየተካሄደብኝ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ያወጣውን መግለጫ የክልሉ መንግሥት አስተባብሏል።

በአማራ ብሔራዊ ክልል የተቀነባበረ የማፍረስ ዘመቻ እየተካሄደብኝ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ያወጣውን መግለጫ የክልሉ መንግሥት አስተባብሏል።

የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ክልላቸው ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የተለየ ፀብ እንደሌለው አመልክተው ሕግን ተላልፎ የሚገኝ ማንም አካል ግን ይጠየቃል ብለዋል።

የፍርድ ሂደቶች ይዘገያሉ፤ ይጓተታሉ መባሉን ያላስተባበሉት አቶ ንጉሡ በዚህ መሥክ የማሻሻያ ሥራዎች መከናወን እንዳለባቸው እንደሚያምኑ አቶ ንጉሡ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት በስተያ በዘጠኝ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ባሕር ዳር በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት በክልሉ አቃቤ ሕግ በተመሠረተው የወንጀል ክሥ የተጠቀሱ አንቀፆች በሃገሪቱ ከፍተኛውን ቅጣት የሚያስከትሉ መሆናቸውን የሕግ ባለሙያው አቶ ተማም አባቡልጉ በሰጡት ትንታኔ ጠቁመው “በድንጋጌው ውስጥ የተጠቀሱትን ጥፋቶች ለመፈፀም የሚያስችል አቅም ያለው የተደራጀ ኃይል ኢሕአዴግ ብቻ ነው” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታና የመንግሥት ምላሽ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምላሽ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት የባህርዳር ክስ ላይ የሕግ ባለሞያ ትንታኔ