“ምዕራቡ ዓለም ዩክሬንን አይዘነጋም” - ባይደን

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

“ምዕራቡ ዓለም ዩክሬንን አይዘነጋም” - ባይደን

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተባበሩት ኃይሎች ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የገቡበትን 80ኛ ዓመት ለማሰብ በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመዋል። በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የተከናወነውን ትልቁን ውጊያ ለማስታወስ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተናገሩት ባይደን፣ የሩሲያ ወረራን ለመመከት በአንድነት መቆም እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል ከኦማሃ ባሕር ዳርቻ፣ ኖርማንዲ፣ ፈረንሣይ የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።