ካማሺ ውስጥ በተከፈተ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ካማሺ ውስጥ በተከፈተ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሶጌ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ “ታጣቂዎች ሦስት ሰው ገድለው ንብረት አወድመዋል” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ጥቃቱን የከፈቱት የኦሮሞ ነፃነት ጦር ታጣቂዎች እንደሆኑና ሌሎች ሦስት ሰዎችን ማቁሰላቸውን የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞትሌ እምዬ ጠቅሰው “ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል በመግባቱ አካባቢው ተረጋግቷል” ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ጦር ቃል አቀባይ ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ “ተገደሉም፣ ቆሰሉም የተባሉት ውጊያ ላይ የነበሩ ወታደሮች ናቸው” ብለዋል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምዥጋ ወረዳ ሶጌ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ (ታህሳስ 20 / 2016 ዓ.ም) ንጋት ላይ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት ቁጥራቸውን በውል ያላረጋገጡት ያልታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን አቶ ተሰፋለም አመኑ እንደሚባሉና የከተማዪቱ ነዋሪ መሆናቸውን ለቪኦኤ በስልክ ገልፀዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመንግስት እና ታጣቂዎች መሀከል በተከፈተ ተኩስ ሰዎች ተገደሉ

የምዥጋ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞትሌ እምዬ “ሸኔ ናቸው” ያሏቸው ታጣቂዎች ቅዳሜ ንጋት ላይ እየተኮሱ ወደ ሶጌ ከተማ እንደገቡና ሦስት ሰው ገድለው ሌሎች ሦስት ሰዎችን ማቁሰላቸውን አመልክተዋል። በወቅቱ “በቂ የመንግሥት ኃይል ከተማዪቱ ውስጥ አልነበረም” ብለዋል።

አጥቂዎቹ “ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የመንግሥት ንብረት አውድመዋል፤ ሁለት ባንኮችን ዘርፈዋል” ብለዋል።

ከጥቃቲ በኋላ መከላከያ መግባቱንና ከተማዪቱ አሁን መረጋጋቷን ገልፀዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በካማሽ ዞን በሎ ጀገንፎይ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ውንጀላው የቀረበበት የኦሮሞ ነፃነት ጦር ዓለምአቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የሚገልፁት ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩት ኦዳ ተርቢ ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ ሰጥተዋል "እርምጃ መውሰዳችን እውነት ነው። ሦስት ሰዎች ተገድለዋል ለተባለውና እኛ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንዳተኮርን ተደርጎ የተገለፀው ትክክል አይደለም። እዚያ የተጎዱት የመንግሥት ኃይሎች እንጂ ሰላማዊ ሰዎች አይደሉም። ወደመ የተባለውም ወታደሮች የመንግሥት ንብረት የሥርዓቱ ጦር ንብረት ነው" ብለዋል።

በመንግሥትና በኦሮሞ ነፃነት ጦር መካከል ሲደረግ የነበረው የሰላም ንግግር ያለ ስምምነት ከተበተነ በኋላ በመካከላቸው ውጥረቱ እየጨመረ መምጣቱ ይሰማል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡